tg-me.com/nibab_lehiwot/174
Last Update:
እኔ እና አንተ.......
በዘመን በቅለን ከአንድ ውሃ ፈልቀን፣
በአንዲት ጨረቃ በፀሀይ ምለን፣
እንዳንለያይ ቃል የተጋባን፣
ዘመን ያፈራን አንድ አይነት ነበርን ፤
እኔ እና አንተ
እንደ ውቅያኖስ ሰፍተን የጠለቅን፣
እንደ ክዋክብት ከእልፍ የበዛን፣
እንደ አሸዋ ከቁጥር የላቅን፣
በአንድ ወቅት የነበርን አበቦች ነበርን፣
እኔ እና አንተ
በመኖራችን የተኗኗርን፣
በደስታችን ሀሴት ያደረግን፣
የተለያየን አንድ አይነት ነበርን፣
እኔ እና አንተ
የአለምን ውበት ጠልቀን የቀመስን፣
የነፍስ እስትንፋስ አብረን እፍ ያልን ፣
ከእውነት ጋራ በክንፍ የበረርን፣
ዘመን ያፈራን ውብ ፍሬ ነበርን።
ግን
እኔ እና አንተ አንድ አይነት እንጅ አንድ ስላልሆንን፣
ተሰበረና እህል ውሃችን፣
ደፈረሰብን ባንድ ያፈለቀን ንፁህ ውሃችን፣
ብርሀን ነፈገች ያማማለችን ውብ ጨረቃችን፣
ጥልቁ አሰመጠን ውቅያኖሳችን፤
ድንገት ጠፉብን ክዋክብቶቻችን፣
ጠወለጉብን አበቦቻችን፣
መደሰታችን ለሀዘን ሆነብን፣
ተለያየና እህል ውሃችን፣
ተበታተንን አንድ አይነት እንጅ አንድ ስላልሆንን ።😉
✍bee
BY ሕይወትን - በገፅ
Warning: Undefined variable $i in /var/www/tg-me/post.php on line 283
Share with your friend now:
tg-me.com/nibab_lehiwot/174